ይህ፡ ማኒ ፍሮም ስዊድን/Money from Sweden ነው

ማኒ ፍሮም ስዊድን/Money from Sweden ወደውጭአገርየሚላኩትንክፍያዎችእናየውጭምንዛሪዎችን የሚያነጻጽር የመንግስት የገንዘብድጋፍያለው ወብሳይት ነው።በስዊድንውስጥወደውጭአገርለመላክየሚያስችሉብዙባንኮች፡ ኩባንያዎች፡ ወኪሎችእናሌሎችየገንዘብተቋማትአሉ። የእኛተልዕኮለእርስዎርካሽእናፈጣንአገልግሎትማግኘትእንዲችሉ ማድረግ ነው። ወብሳይቱ ኣይከፈልበትም፡ እንዲሁምበገበያውከሚገኙት ተጠቃሚዎችነጻ ነው፡ የሚመራውም በሸማቾች ኤጀንሲ ነው።

መነሻ

ግባችን፡ ገንዘብ ወደ ውጭ ሀገር ለማስተላለፍ በምናደርገው ስራ ላይ ግልጽነትና ፍትሃዊ ውድድርን በገበያ ላይ ማራመድ ነው፥ ማለት እንደ ሃዋላ ወይም እንደ ረሚታንስ የሚታወቁ ተግባራት።  

በተጨማሪም፡ ሰዎች ለቤተሰቦቻቸውና ለዘመዶቻቸው ገንዘብ በመላክ፡ በብዙ የዓለማችን ክፍሎች፡ እድገትን ለማምጣት ለሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና ትኩረት መስጠት እንፈልጋለን።

የሸማቾች ኣጀንሲ ኣገልግሎት የሆነው ማኒ ፍሮም ስዊድን፡ ተልእኮው በመንግስት የተሰጠ ነው፡ መንግስቱም ራሱ ተልእኮውን ከተባበሩት መንግስታት ያገኘው ነው። የዓለም ባንክ እና የተባበሩት መንግስታት፡ ገንዘብ ወደ ውጭ መላክ በጣም ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅ መሆኑን ተገንዝበዋል። ስለዚህ የዋጋ ንጽጽር አገልግሎት በመስጠት፡ ወጪውን ተቀንሶ ተቀባዮቹ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲደርሳቸው ይጥራሉ።