የባንክ ሂሳብ መክፈት

በስዊድን ያሉ ባንኮች የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱለዎት ይገደዳሉ። ምንም እንኳ የስዊድን የግል መለያ ቁጥር ባይኖረዎትም፣ የስዊድን አድራሻ ወይም ጥብቅ መለያ ቢኖረዎትም የባንክ ሂሳብ የመክፈት መብት አለዎት። ነገር ግን የእርሰዎን ባንክ ሂሳብ ለመክፈት ባንኩ የእርሰዎን ማንነት ማጣራት አለበት ።

ቀደም ብሎ ከባንኩ በነበረዎ ግንኙነት እምነት ካጎደሉ ባንኩ የባንክ ሂሳብ መክፈቱን ሊከለክለዎት ይችላል። ወንጀልን በተመለከተ ጥርጣሬ ካለም የባንክ ሂሳብ መክፈቱን ሊከለክለዎት ይችላል።

ባንኮች የብይነመረብ/ኢንተርኔት ባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ ማመቻቸት ላይጠበቅባቸው ይችላል። ወይም የመገበያያ ደቢት ካርድ ወይም ከባንክ ብድር ለመውስድ መስፈርት የለም። ምንም እንኳ፣ የስዊድን የፋይናንስ ቁጥጥር ባለስልጣን ባንኮች እንደ የመገበያያ ካርዶች እና የበይነመረብ/ኢንተርኔት ባንክ አገልግሎትን ለደንበኞቻቸው እንዲሰጡ ቢያሳስብም።

ማንነተዎን እንዴት ያሳያሉ?

በስዊድን የሚሰሩ የመታወቂያ ሰነዶች :-

 •የስዊድን የመንጃ ፈቃድ

 •የስዊድን ሀገርአቀፍ መታወቂያ

 •SIS-ምልክት ያለባቸው የመታወቂያ ካርዶች፣ የአውሮፓ የጤና መድህን ካርድ

 •የስዊድን ፓስፖርት

 •የውጭ ሀገር ፓስፖርት

የውጭ ሀገር ፓስፖርት ከተጠቀሙ፣ ባንኩ አንዳንድ ጊዜ ከሀገረዎ ባንክ የእርሰዎን ማንነት የሚገለጽ ደብዳቤ ሊፈልግ ይችላል።

ስለዚህ የበለጠ መረጃ በ www.konsumenternas.se ማግኘት ይችላሉ።