በጣም በዝቅተኛ ዋጋ እንዴት ገንዘብ መላክ እችላለሁ?

እርሰዎ ገንዘብ በሚያስተላልፉበት ወቅት ኩባንያዎች ውስን ቁጥር ያላችው የተለያዩ ክፍያዎችን ያስከፍላሉ።ኩባንያዎች የሚያስከፍሉትን ክፍያዎች እርስ በርሳቸው በማነጻጸር ገንዘብ መቆጠብ ይችላሉ። ምርጡን አማራጭ በመምረጥ፣ ለሚልኩለት የበለጠ ገንዘብ ይደርሳል።

   

ትኩረት ይስጡ:

 •ብዙውን ጊዜ አንድ ትልቅ መጠን ማስተላለፍ ብዙ ባለ ትናንሽ መጠኖችን ከማስተላለፍ ይረክሳል።

 •እሰከመጨረሻው ደቂቃ ድረስ አይጠብቁ፤ በአብዛኛው ለማስተላለፍ ጥቂት ሰዓታት የሚወስድ ለማስተላለፍ ጥቂት ቀናትን ከሚወስድ በጣም ውድ ነው።

 •የተለያዩ የማስተላለፊያ አማረጮችን ያነጻጽሩ

ድርጅቶችን እና ዋጋዎችን ያነጻጽሩ

ልዩነቱ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ ለማየት የእኛን ዋጋ ማነጻጸሪያ ይጠቀሙ። እዚህ ምን ያህል ትልቅ የገንዘቡ ድርሻ  በክፍያዎች እንደሚበላ፣ በ SEK እና በመቶኛ ማየት ይችላሉ። 1,000 SEK እና 3,000 SEK ለመላክ ምን ያህል ወጭዎች እንደሚያስወጣ እናሳየዎታለን። እነዚህ ምሳሌዎች ልዩነቱን እርሰዎ በቀላሉ እንዲመለከቱ ለማሳየት ያለሙ ናቸው። የእራሰዎን መጠን ማስገባት አይቸሉም።