አንድ ነገር ከተሳሳተ

አንድ ነገር ቢሳሳት የትኞቹ ደንቦች እንደሚተገበሩ ኩባንያውን ለመጠየቅ አይፍሩ። የእርሰዎን የገንዘብ ማስተላለፍ የሚያረጋግጡ የትኞቹ መዝገቦች፣ ሰነዶች ሊያስፈልገዎ እንደሚችል ደግሞ ይጠይቁ። ገንዘቡን መላከዎትን ለማረጋገጥ የትኞቹ ደረሰኞች ወይም ውሎች እንደሚያስፈልገዎ ማወቅ አስፈላጊ ነው።

ትኩረት ይስጡ:

 •ተቀባዩ ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን መቀበሉን እስከሚያውቁ ድረስ ያስተላለፉበትን ውሎችና ደረሰኞች ሁልጊዜ ያስቀምጡ።

 •ተቀባዩም ማንኛውም ደረሰኞች ማስቀመጡ ጠቃሚ ነው።

ማንኛውም ችግሮች ካሉ፣ ሁሎችንም ሰነዶች መኖራቸው ማስተካከያ እንዲደረግ ለመጠየቅ፣ ማለትም አብዮቱታ ለማቅረብ አስፈላጊ ናቸው።