ገንዘብ ለመላክ ምን ያህል ወጭ ያስወጣል?

እያንዳንዱ ኩባንያ የራሱን ክፍያ ስለሚያዘጋጅ ወደ ውጭ ሀገር ገንዘብ የመላኪያው ወጭ ብዙውን ጊዜ ይለያያል። ወደ ውጭ ሀገር ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች ለዚሁ አገልግሎታቸው ክፍያ ያስከፍላሉ። የገንዘብ ማስተላለፉ እንዳለቀ፣ ወደተቀባዩ ሀገር ገንዘብ ለመመንዘር ደግሞ ክፍያ አለው። የእነዚህ ክፍያዎች መጠን በአብዘኛው በሰፊው ይለያያል።

ለሁለቱም ለቋሚ ከፍያዎች እና ለገንዘብ ምንዛሬ ምን ያህል እንደተከፈለ መመልከተዎን ያስታውሱ። ለአንደኛው ዝቅተኛ ክፍያ የሚያስከፍል ኩባንያ ለሌላኛው በጣም ከፍተኛ ክፍያዎችን ሊያስከፍል ይችላል።

ሁልጊዜ ገንዘብ ለማስተላለፍ ሲያስቡ በተቀባዩ ሀገር ማናቸውም ክፍያዎች መኖራቸውን ይጠይቁ። ሁሉንም ወጭዎች አንድ ላይ መደመረዎን ያስታውሱ።  ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ምን ያህል ገንዘብ በተቀባዩ እጅ መድረሱ ነው።

 

የሚደመሩ:

 •ክፍያ

 •ከፍያ ለገንዘብ ለመመንዘር፣ ማለትም የምንዛሬ ለውጥ ክፍያ

 •ገንዘቡን ለመቀበል ወጭዎች