ይህ ገንዘብ ከስዊድን ነው

If you are having trouble reading this text you are probably using an IOS device (Iphone, Ipad or Mac computer). The font for this language is not supported. Please use another device to be able to read this text.

ገንዘብ ከስዊድን በመንግስት-ገንዘብ የሚደገፍ የድረ መረብ  አገልግሎት ሲሆን ወደ ወጭ የሚላኩ ክፍያዎችንና የምንዛሬ መጠኖችን ያነጻጽራል። በስዊድን ውስጥ ወደ ወጭ ሀገር ገንዘብ መላክ የሚያስችልዎት ብዙ ባንኮች፣ ኩባንያዎች፣ ወኪሎችና ሌላ የገንዘብ ተቋማት ይገኛሉ። የእኛ ተግባር ለእርሰዎ ምርጥ እና እጅግ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ነው። የድረ መረብ አገልግሎቱ ነፃ፣ በገቢያው ውስጥ ካሉ ሁሉም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ ገለልተኛ  እና በስዊድን የሸማቾች ድርጅት የሚንቀሳቀስ ነው።

 ዳራ               

 የእኛ ዓላማ ወደ ውጭ ሀገር የሚደረግን የገንዘብ ዝውውርን፣ ወይም ሃዋላ ተብሎ በሚጠራው ገቢያ ውስጥ ግልጽ እና ጤናማ ፉክክርን ማሳደግ ነው።

 በብዙ የአለም ክፍሎች ሰዎች ወደ ቤተሰባቸውና ዘመዶቻቸው ገንዘብ በመላካቸው በእድገት ላይ የሚጫዎቱት ጠቃሚ ሚና ትኩረት እንዲያገኝ እንፈልጋለን።

 የስዊድን የሸማቾች ድርጅት አገልግሎት ገንዘብ ከስዊድን የተመሰረተው በመንግስት በተሰጠው መመሪያ መሰረት ነው። መንግስትም በተዋረድ መመሪያውን የተቀበለው ከተባበሩት መንግስታት፣ የተመድ ነው። የተመድ እና የአለም ባንክ መጠነ ሰፊ ምጣኔ ገንዘብን ወደ ውጭ ሀገር በመለካ እንደሚጠፋ አስተውላዋል። የዋጋ ማነጻጸሪያ አገልግሎቶችን በማቅረብ ፣ የበለጠ ገንዘብ ተቀባዮች እጅ እንዲደርስ አልመዋል።