በዋጋ ማነጻጸሪያ ገጽ ላይ የሚያዩት ይህን ነው

በዋጋ ማነጻጸሪያ ገጽ ላይ እኛ እየፈተሽናቸው ያሉትን በተቀባይ ሀገራት ዋና ዋና የገንዘብ ዝውውር አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎችን ማየት ይችላሉ። ሁለት ምሳሌዎችን እናሳያለን:- የሚያዘዋውሩት 1,000 SEK ወይም 3,000 SEK። የእራሰዎን መጠን መምረጥ አይችሉም።

 አረንጓዴ የሚያሳየው ተቀባዩ ጋር ስንት አንደሚደርስ ነው

 ከተመረጠው ድምር ምን ያህሉ በተጨባጭ እንደሚዘዋወር እናሳያለን። ያንን መጠን ነው በአረንጓዴው ቦታ የሚያዩት። በቀዩ ቦታ፣ ምን ያህሉ በቋሚ ክፍያ እንደተቀነሰና በምንዛሬ ልውውጥ እንደጠፋ ያሳያል። ሁሉም ኩባንያዎች ወደ ተቀባዩ ሀገር ወደሚጠቀምበት ገንዘብ ለመቀየር ክፍያ ያስከፍላሉ።

እያንዳንዱ ኩባንያ ገንዘቡ እሰከሚድረስ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድበት ያመላከተብትን ጨምረን እናሳያለን። ውጤቶችን በእጅግ ፈጣን ወይም በእጅግ ርካሽ ዝውውር ሊያጣሩ ይችላሉ።

 የማስጠንቀቂያ ሦስት ማዕዘን የተደበቁ ክፍያዎችን ያመለክታል

 ያቀረብንለትን ጥያቄ ኩባንያው መመለስ ካለፈለገ፣ ይህኑን በማስጠንቀቂያ ሦስት ማዕዘንና በቃለ አጋኖ ምልክት ተመልክቷል። ያ ማለት የተደበቁ ክፍያዎች ሊኖር ይችላል። ከእነዚህ ኩባንያዎች አንዱን ከመረጡ፣ በትክክል ምን ያህሉ ገንዘበዎ ነው ከስዊድን እርሰዎ እንዲላክ በመረጡበት ቀን እንደሚዘዋወር ይጠይቁ።

 ስለ ኩባንያዎችና አገልግሎቶች የበለጠ ያንብቡ

በእያንዳንዱ ኩባንያ ስር ጠቅ በማደረግ  የበለጠ መረጃ የሚያገኙበት አማራጭ ደግሞ አለ። እዚህ በመረጡት ሀገር ሌሎች የሚሰጡዋቸውን አገልግሎቶች ሊያነቡ ይችላሉ። የበለጠ ለማንበብ ደግሞ የእነርሱን ድህረገጽ አድራሻ እዚህ ያገኛሉ። አሁን በተቀባዩ ሀገር ገንዘቡን ለመሰብሰብ ማናቸውም ተጨማሪ ክፍያ መከፈሉን የምናውቅበት መንገድ የለንም። ኩባንያውን ስለዚህ መጠየቅ ይኖርበዎታል። ስለዚህ የበለጠ እዚህ ያንብቡ፡-ሕጋዊ ኃላፊነት//ሕጋዊ ኃለፊነትን ስለመካድ