መደበኛ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ጠቀሜታ

መደበኛ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች፣ ማለትም ባንኮች እና ወኪሎች፣ አሰራራቸው በስዊድን ህግ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል እንዲሁም ኩባንያዎችም በስዊድን ባለስልጣን አካለት ይመረመራሉ። የአለም አቀፍ የገንዘብ ማዘዋወርን አገልግሎቶች የሚቆጣጠሩ ሕጎችም አሉ። ስለዚህ ነው መደበኛ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን መምረጥ መልካም የሚሆነው፣ እነርሱም በባንክ እና ወኪሎች ይገኛሉ ከግል ግለሰቦች ይልቅ።

ባንኮች እና ወኪሎች ለሚተላለፉ ገንዘቦች ተጠያቂነት አለባቸው። ይህ ተጠያቂነት የገንዘብ ማስተላለፉ በሚደረግበት ወቅት በተቀመጡት ውሎችና ሁነታዎች ተተግባሪነት ተቀምጧል።